የዳይሬክተሩ መልዕክት

ክቡራን የደህረ ገፃችን ተጠቀሚዎች

በቅድሚያ እንኳን ወደ አማራብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የልህቀት ማዕከል ድህረ ገጽ በደህና መጣችሁ፡፡የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የልህቀት ማዕከል በክልሉ ዉስጥ የሙያ ብቃት ምዘና በመስጠት ብቁ ለሆኑት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሠርትፍኬት እንዲሰጥ የተቋቋመ መንግስታዊ ተቋም ነዉ፡፡

የሙያ ብቃት ምዘና ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በየጊዜዉ እያደገ የመጣዉን ገበያዉ የሚፈልገዉን የበቃ የሰዉ ሀይል ፍላጎት ለሟሟላትና በሀገርም ሆነ በክልል ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ላይ አስተዋፅኦ የሚያበረክት ብቁ የሰዉ ኃይል ለማቅረብ ነዉ፡፡

የማዕከሉ ተልኮ በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ሥልጠና በማጠናቀቅ ወደ ስራ አለም ለመቀላቀል የተዘጋጀዉንና በኢንዳስትሪዉ ወስጥ እየሰራ ያለዉን ባለሙያ በሙያ ብቃት ምዘና በማረጋገጥ ገብያዉ በሚፈልገዉ የብቃት ደረጃ በማድረስና ምርትና ምረታማነትን እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን ጥራትን በማሻሻል የተሳለጠ ግብይት መፍጠር ነዉ፡፡ በዚህ ረገድ አብረዉን ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በራችን ክፍት ነዉ፡፡

ስለሆነም ዌብ ሳይታችን ለተጠቃሚዎች ተገቢዉን መረጃ በተለይም ስለሙያ ምዘና ምንነትና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲሁም በየጊዜዉ ተመዝነዉ ብቁ የሆኑተን ሙያተኞች ዝርዝር ማግኘትና ማረጋገጥ የሚቻልበት ነዉ ብለን እናምናለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መረጃዎች በየጊዜዉ የሚሻሻሉና የሚያድጉ እንደሚሆኑ ለደንበኞቻችን ስንገልጽ የምታገኙት መረጃ ለራሳችሁና ለመስሪያ ቤታችሁ እንደሚጠቅም በማመን ነዉ፡፡

መልካም ጊዜ

ተስፋዬ የሽዋስ

ዳይሬክተር